የአፍሪካ ልማት ፈንድ በኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል እና በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ስቴት የሚገኙ ማህበረሰቦችን ከአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ለመጠበቅ የሚረዳ የ9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን ገልጿል።
ክላይሜት ፕሩፍ ዋተር ፎር ፉድ የተሰኘው ይህ ፕሮጀክት በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት ድንበር አካባቢ የሚከሰቱ ተደጋጋሚ የጎርፍ እና የድርቅ አደጋዎችን ለመቋቋም ያለመ ነው ተብሏል።
በፕሮጀክቱ 7 በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ የውኃ አቅርቦት ሥርዓቶች የሚገነቡና የሚታደሱ ሲሆን ይህም በአቅራቢያው ለሚገኙ 80 ሺህ ገደማ ነዋሪዎች ንጹሕ ውኃ ያቀርባል ነው የተባለው።
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ተለዋዋጭ የአየር ንብረት ሁኔታዎችን ለመቋቋም የሚያስችል ግብርናን ይደግፋል የተባለ ሲሆን እነዚህ እርምጃዎች የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግና የአርሶ አደሩን አቅም ለማጠናከር ያለሙ መሆናቸው ተገልጿል።
በዚህም ከ100 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በዘላቂ የግብርና አሰራር፣ በዘመናዊ አመራረት እና ድርቅንና ጎርፍን በሚቋቋሙ ምርጥ ዘሮች አጠቃቀም ላይ ስልጠና የሚያገኙበት መሆኑም ነው የተጠቆመው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
