ትራምፕ በኤየር ፎርስ ዋን ፕሬዝዳንታዊ አውሮፕላኖች ላይ ሆነው ለጋዜጠኞቸ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ኢራን የደረሰባቸውን ከባድ ጥቃት አሁን የሚረዱት ይመስለኛል ያሉ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረገው ድርድርም ዳግም ይጀመራል ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በኢራን ላይ ሲፈጽሙ የቆዩትን ጥቃትም ያቆሙት በቀጠናው በሚገኙ የአሜሪካ ወዳጅ ሀገራት ጥያቄ እና ከኢራን ከራሷ በመጣ ጥያቄ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከኢራን ጋር በሚደረገው ድርድር በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ከስምምነት ላይ እደርሳለሁ ብለው እንደሚያስቡ የተጠየቁት ትራምፕ ሰዎችን የመግደል ሱስ የለብኝም ያሉ ሲሆን ድርድሩ በምን ያህል ጊዜ ውጤት እንደሚያመጣ በጋራ እንመለከታለን ብለዋል፡፡
