ኢትዮጵያ ከቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የምታስተናግደው ጉባዔ ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በጉባዔው ከ47 የአፍሪካ አባል ሀገራት የተወጣጡ የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እና ለጋሾችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች እንደሚሳተፉ ታውቋል።
ለ5 ቀናት በሚዘልቀው ጉባኤው በአፍሪካ የጤና ተደራሽነት ለማስፋት በሚያስችሉ ስትራቴጂዎች ላይ ይስማማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
