የጤና ሚኒስቴር ህብረተሰቡ የቲቢ ምርመራን በአቅራቢያው ማግኘት የሚያስችለው “ኖኘክ ቲቢ ” የተሰኘ አዲስ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ መዋሉን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው የቲቢ ምርመራን ለህብረተሰቡ በአቅራቢያው ለማድረስ የሚያስችለው በምህፃሩ “ኖኘክ ቲቢ ” የምርመራ ቴክኖሎጂ በሚያስተዋውቅ የስልጠና መድረክ ላይ ነው።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር አዲሱ ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ በተመረጡ የጤና ተቋማት ተግባራዊ ሆኖ በቀጣይ በመላ አገሪቱ እንደሚስፋፋ ገልፀዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ቴክኖሎጂው የቲቢ ምርመራ መዘግየትንና ያልተመረመሩ ታማሚዎችን በመቀነስ የቲቢ ቁጥጥርን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ተናግረዋል።
ኖኘክ ቲቢ ” የተሰኘው አዲስ ቴክኖሎጂ የቲቢ ምርመራን ፈጣንና ተደራሽ ከማድረጉም በላይ የታካሚዎችን ጉዞ፣ የናሙና ማጓጓዣና ተደጋጋሚ የጤና ተቋም ጉብኝት በመቀነስ ከሪፈራል ምርመራ ጋር የሚያያዙ ወጪዎችንና መዘግየቶችን ለመቀነስ ያግዛል ተብሏል።መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
