EthiopiaNews

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ብሪታንያ በአፍሪካ ብቸኛ የሆነ የጉዞ ሰነድ መመርመር የሚችል መሳሪያ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓን አስታወቀ።

ይህ የተባለው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የጉዞ ሰነዶችን ቁጥጥር ዘመናዊ ለማድረግ ከብሪታንያ ምክትል አምባሳደር ሉክ ቡሎክ ጋር በተወያዩበት ጊዜ ነው፡፡

የተጭበረበረ ሰነድ ይዞ ለመንቀሳቀስ የሚደረግ የጉዞ ሂደትን በዘመናዊ የፍተሻ መሳሪያ በቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማስጀመር የሚያስችል ዘመናዊ የሆነ የጉዞ ሰነድ መመርመሪያ መሳሪያ ነው ተብሏል።

ዋና ዳይሬክተሯ ሰላማዊት ዳዊት ድጋፉ የቀጠናውን ነፃ የሰዎች ዝውውር በከፍተኛ ጥራት ለመከወን ይረዳናል ብለዋል።

በብሪታንያ የድንበር አስተዳደር እዝ ድጋፍ የተደረገው የጉዞ ሰነድ ማጣሪያ መሳሪያ በቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያለውን ስራ የሚያግዝ እና የአገልግሎቱን ደረጃ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

የብሪታንያ ምክትል አምባሳደር ሉክ ቡሎክ የአየር የድንበር ስራን በጋራ በመስራት ህገወጥ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር እንሰራለን ሲሉ ብለዋል።መረጃው ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተገኘ ነው።