ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡን አስታወቀ።
ባንኩ በዛሬው እለት ባካሄደው የ125 ሚሊየን ዶላር የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 28 ባንኮች መሳተፋቸው ገልፆ 9ኙ ባንኮች ደግሞ በጨረታው ማሸነፋቸውን ይፋ አድርጓል።
በዛሬው የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የተሳተፉ ባንኮች 470 ነጥብ 17 ሚሊየን ዶላር ለመግዛት ፍላጐት እንዳሳዩ ተገልጿል።
ባንኩ ከዚህ ቀደም ባወጣው የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ መርሃ ግብር መሰረት በቀጣይ የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ይደረጋል ብሏል።
ብሔራዊ ባንክ ያለፈው ሰኔ ወር ባካሄደው የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ157 ብር መሸጡ ይታወሳል።
