InternationalNews

የአሜሪካ ብሔራዊ ዕዳ የአርባ ትሪሊዮን ዶላር ጣሪያን በእጅጉ ተጠግቷል።

የአሜሪካ ዕዳ ይሄን ያህል ያደገው ባለፈው አስር ዓመት በፊት ከነበረው በእጥፍ በመጨመር ነው።

ዕዳው እንዲህ ጣሪያ የነካው በአሁኑ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና በቀዳሚው የአሜሪካ መሪ ጆ ባይደን ዘመን ከፍተኛ የመንግስት ወጭ ስለነበር ነው ተብሏል።

በፈረንጆቹ 2016 የአሜሪካ ብሔራዊ ዕዳ ከ20 ትሪሊዮን ዶላር በታች እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የአሜሪካ ኮንግረስ የበጀት ጉዳዮች ቢሮ በፈረንጆቹ 2026 የበጀት ዓመት ሲጠናቀቅ የአገሪቱ ዕዳ 39 ነጥብ 6 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል ሲል ሪፖርት አውጥቷል።

ቢሮው አገሪቱ ሊኖራት ወደሚችለው የ41 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ዶላር የብድር ጣሪያም በፍጥነት እየተጠጋች ሲሆን በፈረንጆቹ 2036 አጠቃላይ ዕዳዋ 64 ትሪሊዮን ዶላር ይሆናል ነው የተባለው።