የሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15.3 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ይህ በሐምሌ 2017 ዓ.ም ከነበረው 13.7 በመቶ ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ ማሳየቱን የጠቀሰው አገልግሎቱ ምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ በ15.7 በመቶ መጨመራቸውን ነው የገለጸው፡፡
በዋናነት አትክልት በ13.6 በመቶ፣ ስጋ በ21.6 በመቶ፣ ፍራፍሬ በ19.2 በመቶ፣ ዘይት በ20.34 በመቶ እንዲሁም ስኳር በ39.4 በመቶ የዋጋ ግሽበት በመኖሩ ይህ ጭማሪ መመዝገቡን አገልግሎቱ ገልጿል።
ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት ደግሞ 14.8 በመቶ መድረሱም ነው የተነገረው፡፡
በትራንስፖርት ዘርፍ ደግሞ 15.6 በመቶ፣ በኮሙዩኒኬሸን 8.0 በመቶ፣ በምግብ ቤቶችና ሆቴሎች 15.6 በመቶ እንዲሁም በሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች የተስተዋለው የዋጋ ጭማሪ 19.3 በመቶ ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል።
የሰኔ ወር 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.9 ሆኖ መመዝገቡ አይዘነጋም፡፡
