EthiopiaNews

በአዲስ አበባ የደንብ መተላለፎች ቀድሞ ከነበረው 81 ከመቶ ቅናሽ አሳይቷል ብሏል የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን፡፡

ባለስልጣኑ ይህን ያለው የ2018 የበጀት ዓመት የሥራ እቅድ አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በመከረበት መድረክ ላይ ነው፡፡

የባለሥልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በ2018 በጀት አመት ዘጠኙን የደንብ ጥሰት ማዕከል በማድረግ ባከናወናቸው ተግባራት የደንብ ጥሰትን በ81 በመቶ መቀነስ ተችሏል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱም ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰራ ስራ በህገወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው የተገኙ ከ5ሺ በላይ አካላት ላይ እርምጃ ተወስዷል የተባለ ሲሆን በአዋኪ ድርጊቶች ላይ ሲሳተፉ በተገኙ 1ሺ 700 ገደማ አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነግሯል፡፡

እንዲሁም ህገወጥ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን በመቆጣጠር ረገድ ከ6ሺ በላይ አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱ የተገለጸ ሲሆን ከህገወጥ መንገድ አጠቃቀም ጋር ተያይዞም ከ2ሺ በላይ ሰዎች እርምጃ ስለመወሰዱ ተመልክቷል፡፡

ህገወጥ የመሬት ወረራን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር ውጤት መመዝገቡን የገለጸው ባለስልጣኑ በዚህም በከተማዋ ህገወጥ የመሬት ወረራን ሙሉ ሉሙሉ ማስቀረቱን ገልጿል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv