EthiopiaNews

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት መሠረት በይፋ ንግድና የወጪ ምርት መላክ ከጀመረችበት መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም  ጀምሮ 14 ነጥብ 66 ሚሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ መመዝገቡን ተነገረ፡፡

አስካሁን ባለው ሁኔታ የገበያ መዳረሻዎች እያደጉ እንደሚገኙ የተገለጸው ጉሙሩክ ኮሚሽን፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ኢጋድና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራርና ባለሙያዎች በተገኙበት ነፃ የንግድ ቀጠና ትግበራውን ይበልጥ ለማሳለጥ እና በትግበራ ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ተጨማሪ የገበያ መዳረሻዎችን ለማስፋት የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት በነጻ ንግድ ቀጠናው ስር ምርቶቻቸውን በብዛት የሚልኩ ላኪዎችን የሚያግዝ ፕሮጀክት በመንደፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽንም ነጻ ንግድ ቀጠናው የተሳለጠ እንዲሆን ለማድረግ በርካታ ሥራዎች መስራቱን እና በቀጣይም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡

በነጻ ንግድ ቀጣናው ትግበራ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት እና የማስፈጸም አቅምን ለማጎልበት የሚያስችሉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚሰጡም ተነግሯል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv