EthiopiaNews

በ2018 በጀት ዓመት የ580 ኪሎ ሜትር አዳዲስ መንገዶች ግንባታ እና 12 ሺህ 882 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የተለያዩ የመንገድ ጥገና ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ይህን ያስታወቀው የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ሲሆን በበጀት ዓመቱ የ238 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ደረጃ ማሻሻል መቻሉንም ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ 24 የመንገድ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸው እና በተያዘው አዲስ በጀት ዓመት ደግሞ ከ1 ሺህ 67 ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶችን ለመገንባት እና ከ16 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የተለያዩ መንገዶችን ለመጠገን አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱ ተመላክቷል።