ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።
የጤና ሙያ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ከነሀሴ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ ሊንክ https://hple.moh.gov.etላይ በመግባትና የብሄራዊ መለያ ቁጥር እና ፓስወርድ በማስገባት የፈተና ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሚኒስቴሩ በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 952 በመደወል ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተናውን ያለፉ ተመዛኞች ከሰኞ ዻጉሜ 2/2018 ዓ.ም ጀምሮ ስም ዝርዝራቸው ወደ ክልል የሚላክ መሆኑን ገልፆ ተመዛኞች የሙያ ፍቃዳቸውን 12ተኛ ክፍል በተማሩበት ክልል ማውጣት ይችላሉ ብሏል።
መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
