EthiopiaNews

የብራዚል የንግድና የኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ ኤጀንሲ አፔክስ ብራዚል በአዲስ አበባ ቋሚ ጽሕፈት ቤቱን ሊከፍት መሆኑ ተገለጸ።

የአፔክስ ብራዚል በአዲስ አበባ ጽህፈት ቤቱን መክፈት በኢትዮጵያና ብራዚል መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ወደ ተጨባጭ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድሎች ለመቀየር የሚያግዝ ስትራቴጂያዊ ድልድይ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያና ብራዚል የብሪክስ አባልነት የሁለቱን ሀገራት የንግድ፣ የቀጥታ ኢንቨስትመንትና የጋራ ኢንዱስትሪያዊ ትብብር ለማሳደግ ተጨማሪ ስትራቴጂያዊ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጠቅሷል፡፡

በዚህም ኮሚሽኑ ከአፔክስ ብራዚል ጋር በአግሪ ቢዝነስና አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በኢንዱስትሪ ማምረቻ፣ በአረንጓዴ ኢነርጂ፣ በሎጂስቲክስና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች ትብብርን ለማጠናከር ዝግጁ መሆኑን ጠቁሟል።

የአፔክስ ብራዚል ቋሚ ጽሕፈት ቤት መቋቋሙ በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድ ትስስርን፣ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቅን፣ የገበያ መረጃ ልውውጥንና የንግድ ትስስርን ለማጠናከር ቋሚ መድረክ ይፈጥራል ነው የተባለው።