የመቄዶንያ በጎ አድራጐት ማህበር ወጣቱ ባለሀብት ምህረትአብ ሙሉጌታ 8.5 ሚሊየን ብር ለማህበሩ መለገሱን አስታወቀ።
ባለሃብቱ የዘመን መለወጫን በማስመልከት ትናንት በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር ዋናው ማዕከል ተገኝቶ አዲስ አበባ እና 57 ቅርንጫፍ ለሚረዱ 9,000 አቅመ ደካማ ወገኖች የምሳ ማብላት መርሃ ግብር ማካሄዱን ማህበሩ ገልጿል።
ለዚህ የምሳ ማብላት መርሃ ግብር 4.5 ሚሊየን ብር የመደበው አቶ ምህረትአብ፣ በተጨማሪም 4 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በአጠቃላይ 8.5 ሚሊየን ብር ለመቄዶንያ አበርክቷል ተብሏል።
አቶ ምህረትአብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን ተቋም ማገዝና መደገፍ እንደሚገባው ጠቁሟል።
የመቄዶንያ መስራች ዶ/ር ብንያም በለጠ በበኩላቸው ምህረትአብ ሙሉጌታ ሁሌም የማዕከሉ ደጋፊ መሆኑን ገልፀዋል።
👉መረጃው ከመቄዶንያ በጎ አድራጐት ማህበር የተገኘ ነው።
