አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ለ3ኛ ጊዜ ለተጨማሪ አራት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ በድጋሚ መመረጣቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል::
ፌዴሬሽኑ ይሄን ያለው ዛሬ እያካሄደው ያለውን 18ኛ መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ነው።
አቶ ኢሳያስ ጅራ ከአጠቃላይ 99 መራጭ 81 ድምፅ በማግኘት ለቀጣዮቹ 4 ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል ።
ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ዶ/ር ዳኛቸው ንግሩ፣ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ ወ/ሮ ሰርካለም ሳሙኤል፣ ዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉሥ፣ አቶ አበባው ሰሎሞን፣ አቶ አንበሴ አበበ እና አቶ ደመላሽ ይትባረክ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ተመርጠዋል።
