ኢትዮጵያ ከ17 ሀገራት ጋር የጀመረችውን የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር እስካሁን ከ11 ሀገራት ጋር መቋጨቷን እና ከቀሩት ስድስት ሀገራት ጋር የሚደረገው ድርድርም ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተካሄደ እንደሚገኝ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አክሎም ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለዓመታት ስታካሂድ የቆየችው ድርድር ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መቃረቡን ተናግሯል፡፡
የአባልነት ሂደቱ በሁለት ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፍሎ በከፍተኛ ትኩረት እየተካሄደ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጾ ሂደቱን ወደ መጨረሻው ረቂቅ የሥራ ቡድን ሪፖርት ደረጃ ማድረስ ተችሏልም ነው ያለው።
