InternationalNews

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፍልስጤም ያቋቋሙት የሰላም ቦርድ፣ በጋዛ ለሚከናወነው የመልሶ ግንባታ ስራ የሚውል የ2 ነጥብ 45 ቢሊዮን ዶላር እቅድ ይፋ አደረገ።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይፋ የተደረገው ይህ በጀት፣ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ለሚከናወኑ የመኖሪያ ቤት፣ የኃይል ማመንጫ እና የጽዳት ፕሮግራሞች ይውላል ተብሏል።

የቦርዱ አመራሮች እስረኞችን በመፈታትና በተኩስ አቁም ስምምነቱ ዙሪያ መሻሻሎች መኖራቸውን ቢገልጹም፣ ሀገራት ቃል የገቡት ገንዘብ በተገቢው ሁኔታ አለመሰብሰቡና የጸጥታ ችግሮች አሁንም ትልቅ ፈተና መሆናቸውን ገልጸዋል።

በጦርነት የወደመችውን ጋዛ ሙሉ በሙሉ መልሶ ለመገንባት በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ ከ71 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሊያስፈልግ እንደሚችል ነው የቦርዱ አባላት ግምታቸውን ያስቀመጡት።

በሌላ በኩል ሀማስ የጦር መሳሪያውን አውርዶ እስራኤል ጦሯን ከጋዛ እንድታስወጣ ቢጠይቅም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግን ሀማስ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እስኪፈታ ድረስ ጦራቸው በጋዛ እንደሚቆይ አስታውቀዋል።