EthiopiaNews

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ስርአትን ለማጠናከር የ68 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ።

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮንዴር ሌየን ይሄን ያሉት በኤክስ የማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሳተላለፉት መልእክታቸው ነው።

ፕሬዚዳንቷ ህብረቱ ለኢትዮጵያ ለመስጠት ቃል የገባው ድጋፍ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ስርአቱን ለማጠናከር የሚውል ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮንዴር ሌየን አፍሪካን ጨምሮ በመላው ዓለም ለሚውል የሰብአዊ ድጋፍ ስራ ከ710 ሚሊየን ዶላር በላይ ህብረቱ ለመለገስ ቃል መግባቱን ተናግረዋል።

ህብረቱ ቃል ከገባው ከአጠቃላይ ድጋፍ ውስጥ 430 ሚሊየን ዶላሩ ለአፍሪካ ነው ተብሏል።