EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ነገ ረቡዕ መስከረም 20/2019 ዓ.ም በይፋ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት ጽ/ቤት ይሄን ያለው ባስተላለፈው የጉባኤ ጥሪ ነው።

ም/ቤቱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የከተማ አስተዳደሩን ወክለው የተመረጡ የምክር ቤት አባላት በሙሉ ነገ ረቡዕ ከጧቱ 2፡00 በአድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲገኙ ጥሪውን አስተላልፏል። መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።