EthiopiaNews

የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉ የመንግሥት ምሥረታ ጉባኤ ነገ መስከረም 21/2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስታወቀ።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ይሄን ያሉት በጉባኤው ዙሪያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ዋና አፈ ጉባኤዋ በመግለጫቸው ምክር ቤቱ 7ኛ ዙር 1ኛ ዓመት መሥራች እና መደበኛ ጉባኤውን ከመስከረም 21 እስከ 22/2019 ዓ.ም ድረስ ያካሂዳል ብለዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ በመጀመሪያው ቀን የመንግሥት ምሥረታ የሚካሄድ ሲሆን፣ በሁለተኛው ቀን ደግሞ የክልሉ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ለምክር ቤቱ ቀርቦ እንደሚጸድቅ አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል፡፡

መረጃው ከአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።