InternationalNews

ቻይና እስከ ፈረንጆቹ 2028 ባለው ጊዜ ውስጥ ታይዋንን በኃይል የመውረር ዕድሏ አነስተኛ መሆኑን የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ የሀገሪቱ ጦር እስከ 2027 ድረስ ለወረራ ዝግጁ እንዲሆን አዝዘው የነበረ ቢሆንም፣ በጦሩ ውስጥ በተካሄደው የጸረ-ሙስና ዘመቻ ምክንያት ዝግጅቱ መዘገየቱ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም ቤጂንግ በፈረንጆቹ 2028 በሚካሄደው የታይዋን ምርጫ ከእሷ ጋር የተሻለ ግንኙነት ያለው አካል ወደ ስልጣን ይመጣል የሚል ተስፋ ማድረጓ የወረራውን ስጋት እንዳራዘመው ተገልጿል።

ነገር ግን በዚሁ ምርጫ አሁን በስልጣን ላይ ያለውና የታይዋንን ሉዓላዊነት የሚደግፈው ፓርቲ በድጋሚ ከተመረጠ፣ ቻይና ከ2028 በኋላ የኃይል እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ተገምቷል።

የአሜሪካ ባለስልጣናት አክለውም፣ ቻይና በአሁኑ ወቅት እንደ ታይዋን ወረራ ያለውን ውስብስብ ወታደራዊ ስምሪት በሙሉ አቅም ለመፈጸም የሚያስችላት ሙሉ ዝግጅት እንደሌላት አብራርተዋል።