EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ ሕፃናት እና አካል ጉዳተኞችን ፍትሕ የማግኘት መብት ለማስከበር ፍርድ ቤቶች ያለ አድሎ ምቹ የችሎት ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንዳለባቸው አሳስቧል።

ኢሰመኮ በአማራ ክልል ለሚገኙ ፍርድ ቤት ዳኞች የሴቶች፣ የሕጻናት እና የአካል ጉዳተኞችን ፍትሕ የማግኘት መብት በማስከበር በሰጠው ስልጠና ዳኞች ውሳኔ በሚሰጡበት ወቅት ለሕፃናት በጎ እድል ቅድሚያ መስጠት አለባቸው ነው ያለው።

ሴቶት እና ህፃናት እድሜያቸውን እና ጾታቸውን መሠረት ያደረገ አድሎ ሳይደረግባቸው ፍትሐዊ የሆነ የሕግ አገልግሎት ድጋፍ እና ግንዛቤ ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን ማረጋገጥ ይገባልም ነው የተባለው፡፡

በተመሳሳይ የአካል ጉዳተኞች መብት ለማስጠበቅ ፍርድ ቤቶች የአካባቢ ምቹነትን ማረጋገጥ እና የቋንቋ ተግዳሮቶችን መፍታት እንዳለባቸው የተገለጸ ሲሆን የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን በመመደብ ተቋማዊ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑም ተጠቅሷል።