EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመትም በከተማዋ የሚታዩ የደንብ መተላለፎችን በ77.33 በመቶ መቀነስ መቻሉን አስታወቀ።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ይሄን ያለው በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ አበይት ተግባራት በተመለከተ በሰጠው መግለጫ ነው።

በሩብ ዓመቱ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባደረገው የተቀናጀ እንቅስቃሴ በከተማዋ የመሬት ወረራን መቶ በመቶ መከላከል መቻሉን እና ሌሎች የደንብ መተላለፎችም በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንሱ መደረጉ ተገልጿል።

አዲስ አበባ የደንብ መተላለፍ በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰባትና ለኑሮ ምቹ ከተማ ለማድረግ የኅብረተሰቡ ሚና ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይም የሕዝብ ግንዛቤን የማሳደግ ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።