የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቱሪዝም መዳረሻ እና የንግድ ማዕከል ወደ ሆነችው ናካላ ከተማ በሳምንት ሦስት ጊዜ የሚደረግ አዲስ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት ጀመረ።
ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2019 አ.ም በይፋ የተጀመረው ይህ አዲስ በረራ አህጉራዊ ትስስርን ከማጠናከሩም በላይ ለቱሪዝም እና ቢዝነስ እድገት የላቀ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
በረራው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር አስፈላጊ ሚና አለው የተባለ ሲሆን በተለይም የቱሪዝም፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማሳለጥ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው በማስጀመሪያው መርሃ ግብር ላይ ተጠቁሟል።
የአየር መንገዱ ይህ የናካላ በረራው በሞዛምቢክ ሦስተኛ መዳረሻው ሲሆን ከዚህ ቀደም ማፑቶና ቤይራ ከተሞች ላይ ይበር እንደነበርም ተገልጿል።
