EthiopiaNews

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በተያዘው የፈረንጆቹ 2026 አመት 9 ወራት ውስጥ የኢትዮጵያ እና የሩሲያ የንግድ ልውውጥ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ተናገሩ።

ፕሬዚዳንት ፑቲን ይሄን ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በክሬምሊን ቤተመንግስት ባካሄዱት ውይይት ላይ ነው።

የሩሲያው መሪ ፑቲን ባለፉት 9 ወራት የተመዘገበው የሁለቱ ሃገራት የ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር የንግድ ልውውጥ ከፈረንጆች 2025 አመት ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ ያደገ ነው ብለዋል።

“ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በጋራ ይቆማሉ፤ በተባበሩት መንግሥታት፣ በብሪክስ እና በተለያዩ ሌሎች መድረኮች ላይ ጠንካራ ውይይት መሥርተናል” ሲሉ ፑቲን ገልጸዋል።

መረጃው ከክሬምሊን ቤተ መንግስት የተገኘ ነው።