የሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የነባር የመንግሥት ተሽከርካሪዎች በአዲሱ “ETH” ሰሌዳ የመቀየር አገልግሎት እስከ ጥቅምት 30 , 2019 ዓ.ም እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው የነባር የመንግሥት ተሽከርካሪዎች የመለያ ቁጥር ሰሌዳ ቅያሬን አስመልክቶ ባወጣው ማስታወቂያ ነው።
የከተማ አስተዳደሩ የአሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አዲሱን “ETH” የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ ከሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለአዲስ ተሽከርካሪዎች ምዝገባ ተግባራዊ ማድረጉን ሚኒስቴሩ አስታውሷል።
ሚኒስቴሩ በፌዴራል ሚኒስቴር መ/ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት የተመዘገቡ፣ ኮድ 4 የመንግሥት ሰሌዳ ያላቸው ነባር ተሽከርካሪዎች የመለያ ቁጥር ሰሌዳቸውን በአዲሱ “ETH” ሰሌዳ የመቀየር አገልግሎት ጥቅምት 17 የተጀመረ መሆኑን ገልፆ አገልገሎቱ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል ብሏል።
ስለሆነም ተቋማቱ የተሽከርካሪ ፋይላቸው በሚገኝበት የባለሥልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመቅረብ የሰሌዳ ቅያሬ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
መረጃው ከሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
