የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በጥቅምት ወር ብቻ ከ1,140 በላይ ደንብ የተላለፉ ግለሰቦችና ተቋማቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ይሄን ያለው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እና የደንብ መተላለፍን ለመቀነስ ያለመ የውይይት መድረክ ላይ ነው።
በውይይቱ ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ጠንካራ የቁጥጥር ሥራዎች መከናወናቸውን በከተማዋ ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት እንዲረጋገጥና በወንዝ ዳርቻዎች ልማት አካባቢዎች በሚገኙ መሠረተ ልማቶች ጥበቃ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር መደረጉ ተገልጿል።
ባለስልጣኑ በጥቅምት ወር ብቻ 100 ድርጅቶች እና 1,040 ግለሰቦች (በጠቅላላው 1,140 ሕግ ተላላፊዎች) ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።
በዚህም ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ አስተዳደራዊ ቅጣት ተጥሎ ለፋይናንስ ገቢ መደረጉን ባለስልጣን መ/ቤቱ አስታውቋል።
