ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ከ90 በመቶ በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቷ ከውሃ የሚመንጭ መሆኑን ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት በቱርክ አንታሊያ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው 31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ነው።
ከ90 በመቶ በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቷ ከውሃ የሚመንጭ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ንጹህ ኃይል ለጎረቤት ሀገራትም ጭምር የሚቀርብ መሆኑን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በኤልኒኖ ምክንያት የሚከሰተውን ድርቅ እና ጎርፍ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ በቅድመ-ማስጠንቀቂያ ላይ ተመስርታ እየሰራች እንደምትገኝም በመድረኩ ገልፀዋል።
በአካባቢ ጥበቃ ረገድ ኢትዮጵያ የነዳጅ እና ዲዚል ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በማድረግ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የመሸጋገር ሀገራዊ እርምጃ መወሰዷንም ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2027 የሚካሄደውን የኮፕ 32 የአየር ንብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ የምታስተናግድ በመሆኑ፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ልዑካን ወደ ሰው ዘር መገኛ ኢትዮጵያ እንዲመጡም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመድረኩ ጥሪ አቅርበዋል።
