የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአውሮፓ ተወካዮች በቀጣዩ የዩክሬን የሰላም ድርድር ላይ እንዲሳተፉ መስማማታቸውን የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ አስታወቁ።
ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ በሞስኮ ከፑቲን ጋር ከተወያዩ በኋላ እንደገለጹት የአውሮፓ አገራት አጋሮች በመሆናቸው በቀጣዩ ስብሰባ መሳተፋቸው እጅግ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ሞስኮ ለውይይት ዝግጁ መሆኗን ቢገልጹም አውሮፓውያን ግን በዩክሬን ሰላምን ወይስ ጦርነትን እንደሚፈልጉ ዋሽንግተን አጣርታ እንድታሳውቃቸው ጠይቀዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ የአውሮፓውያንን ተሳትፎ በደስታ የተቀበሉ ሲሆን ቀጣዩ ውይይት የተኩስ አቁም እና ግጭትን የማርገብ አጀንዳዎችን እንዲያካትት ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዜሌንስኪ በጦር ግንባር የሚጠቀሙበት የአሜሪካ የሳተላይት ግንኙነት አገልግሎት መስተጓጎሉን የገለጹ ሲሆን በሃገራቱ መካከል የግዛት ይገባኛል ጥያቄው አሁንም ዋነኛ ልዩነት ሆኖ ቀጥሏል።
