የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በዳካር የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ብሔራዊ ኩራት ለሆነው የልዑካን ቡድን የ16 ሚሊየን ብር ሽልማት አበረከተ።
በዳካሩ የወጣቶች ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ላመጡት አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ሽልማት ሲበረከትላቸው፣ የብር ሜዳልያ ላመጡ አትሌቶች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው የ750ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በጋራ ለአትሌቶችና ለአሰልጣኞች እንዲሁም ለልዑክ ቡድኑ አባላት የ30 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት አበርክተዋል።
ኢትዮጵያ በዳካር በተካሄደው የወጣቶች ኦሎምፒክ 5 ወርቅ፣ 3 ብር በአጠቃላይ 8 ሜዳሊያ ማስመዝገቧ ይታወቃል።
መረጃው ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
