InternationalNews

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው ሺ ጂንፒንግ እና ከሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ጋር  ዛሬ በቻይና ሼንዘን ከተማ በሚያደርጉት የሶስትዮሽ ስብሰባ የኒውክሌር መሣሪያ ቁጥጥር እንዲሁም የዩክሬንና የኢራን ጦርነቶች ዋና አጀንዳዎች መሆናቸው ተገለጸ።

ከሶስትዮሽ ውይይቱ አስቀድሞ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሺ ጂንፒንግ ጋር ለአንድ ሰዓት ያህል ተወያይተው ቻይና ተጨማሪ የአሜሪካ የግብርና ምርቶችን እንድትገዛ የጠየቁ ሲሆን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ የነዳጅ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ባላቸው የጋራ ፍላጎት ላይ መምከራቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም ትራምፕ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ባለፈው ዓመት በአላስካ ከተገናኙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ40 ደቂቃዎች ያህል የፊት ለፊት ውይይት ያደረጉ ሲሆን መልካም ውጤት እንደሚጠብቁ አስታውቀዋል።

ባለፈው የካቲት ወር ያበቃውን የኒውክሌር ስምምነት ቻይናን ባካተተ አዲስ ውል ለመተካት ትራምፕ ቢፈልጉም የዘርፉ ባለሙያዎች ግን በአንድ ስብሰባ ብቻ ፈጣን ለውጥ ይመጣል ብለው እንደማይጠብቁ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ እና ቻይና በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በንግድ ሚዛን ዙሪያ ያላቸው ውጥረትም የስብሰባው ሌላኛው አንኳር ጉዳይ ሆኗል።