EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች ለ2019 አ.ም የሚከፍሉት የመጀመሪያው የቅድመ ግብር ክፍያ የመክፈያ ጊዜ ህዳር 30 2019 አ.ም የሚጠናቀቅ መሆኑን አስታወቀ።

ቢሮው ይሄን ያለው የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮችን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።

ቢሮው ለደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች በአጭር ፅሁፍ በሚላክ የክፍያ ማዘዣ መሰረት ግብር ከፋዮቹ የግብር ክፍያቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም በቴሌ ብር እንዲከፍሉ አሳስቧል።

የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የሚከፍሉት ቅድመ ግብር ክፍያ በሐምሌ ወር 2019 አ.ም ከሚከፍሉት አመታዊ የግብር ክፍያ ላይ የሚታሰብ ወይም የሚቀነስ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል።

ቢሮው ከህዳር 30 2019 አ.ም በኋላ የሚመጡ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች ላይ ቅጣት እንደሚጣል አስጠንቅቋል።