EthiopiaNews

5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይሄን ያለው ጉባኤውን አስመልክቶ ባወጣው አጭር መግለጫ ነው።

በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ፣ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው ተብሏል።

“የአፍሪካ የጤና ደህንነት እና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነት እና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነት እና ጽናት የሚደረግ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል ጉባኤው በመካሄድ ላይ ነው።

ይሄው ጉባኤ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማእከል አፍሪካ ሲዲሲ በጋራ የተዘጋጀ ነው።