InternationalNews

የአሜሪካው የጦር ሚኒስቴር ከጎረቤት ካናዳ ጋር ያለው ወታደራዊ ትብብር ዝቅ እንዲል የውስጥ መመሪያ አስተላለፈ።

ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው የጦር ሚኒስትሩ ፒተር ሄግዝ ከእንግዲህ ከካናዳ ጋር የሚደረገው ወታደራዊ ትብብር እንዲቀንስ ሚስጢራዊ የውስጥ ደብዳቤ ለመስሪያ ቤታቸው የሥራ ኃላፊዎች ልከዋል።

የኔቶ ወታደራዊ ቃልኪዳን መስራቾች የሆኑት ሁለቱ ሀገራት በተለይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በእጅጉ ሻክሯል።

የመቃቃሩ መንስኤል ትራምፕ ካናዳን ጠቅልሎ 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት አደርጋለሁ ማለታቸውና ተከታታይ ታሪፍ በካናዳ ላይ መጣላቸው ነው።

ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው አሜሪካ ወታደራዊ ትብብሩን ማላላቷ ካናዳ እርምጃውን እንደ ክህደት ልትቆጥረው የሚያደርጋት ነው።