EthiopiaNews

ብሔራዊ ባንክ በዛሬው እለት የ140 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ባንኩ ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።

በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል ፍላጎቱ ያላቸው ባንኮች እንዲሳተፉ ብሔራዊ ባንክ ጥሪውን አቅርቧል።

ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ሳምንት በፊት ባደረገው የ140 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን ዶላር በ159 ብር ከ70 ሳንቲም መሸጡ ይታወሳል።

በዚሁ ጨረታ ከተሳተፉት 31 ባንኮች ውስጥ 26ቱ አሸናፊ መሆናቸው የሚታወስ ነው።

መረጃው ከብሔራዊ ባንክ የተገኘ ነው።