EthiopiaInternationalNews

በመቐለ ከተማ ከጥቅምት 27 ቀን 2019 ጀምሮ በተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ማሻሻያ እንደተደረገበት የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር ገለጸ፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ የከተማዋ የሰላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን የገለጸው አስተዳደሩ በዚህም መሰረት በቀደመው መመሪያ ውስጥ ምሽት 2 ሰአት የነበረው የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የሰአት ገደብ ወደ ምሽት 4 ሰአት መዛወሩ ተገልጿል፡፡

ሆኖም፣ በባጃጆችና በሞተር ሳይክሎች ላይ የተጣለው እገዳ እስከ ምሽቱ 2ድረስ ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው የተገለጸው፡፡

በሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች እና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ያለ ገደብ ለ24 ሰዓታት አገልግሎት እንዲሰጡ መፈቀዱንም አስተዳደሩ ጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል አስተዳደሩ ነዳጅ ወደ መቐለ ከገባ ከአንድ ሳምንት በላይ ማስቆጠሩ ጠቅሶ የንግድና የትራንስፖርት ዘርፎችን በማቀናጀት የመጣውን ነዳጅ ከዛሬ ጀምሮ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የትግበራ እቅድ መውጣቱንም ገልጿል፡፡