EthiopiaNews

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው አንድ አመት በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ120 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው መመለሳቸውን አስታወቀ።
‎
‎ከመስከረም 5/2018 ዓ.ም ጀምሮ ያሳለፍነው ሳምንት ድረስ በአምስተኛው ዙር ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ በአጠቃላይ 120 ሺህ 205 ዜጎችን በማምጣት መጠናቀቁን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

‎ከተመለሱት ዜጎች መካከል 105 ሺህ 470 ወንዶች፣ 13 ሺህ 482 ሴቶች እና 1 ሺህ 253 ሕፃናት ሲሆኑ፣ 4 ሺህ 989 የሚሆኑት ደግሞ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።

‎የመመለስ ሥራው በተለይም በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሕይወትና ደህንነት ቅድሚያ በመጠበቅ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የሚደረገው ቀጣይነት ያለው ጥረት አካል ነው።

‎ለተመላሽ ዜጎች በሚደረገው ጥበቃና ድጋፍ በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት አስፈላጊውን እንክብካቤና ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማቀላቀል ሥራዎች ተከናነዋል።