EthiopiaNews

በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች የባንክ አክስዮን በብር መግዛት እንዲችሉ የሚፈቅድ ረቂቅ መመሪያ ብሔራዊ ባንክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ባንኩ ይሄን ያለው ከቀናት በፊት በድረ ገፁ ባወጣው ረቂቅ መመሪያ ላይ ነው።

ረቂቅ መመሪያው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች የባንክ አክስዮን በብር መግዛት እንዲችሉ ይፈቅዳል።

ይሁን እንጂ ከሃገር ውስጥ ባንኮች አክስዮኖች የገዙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኢንቨስት አድርገው ያገኙትን ገቢ በውጭ ምንዛሬ ማውጣት እንደማይችሉ መመሪያው ይጠቅሳል።