EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ116 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ መስመር መልሶ ግንባታና ማሻሻያ ሥራ 92 በመቶ መጠናቀቁን አስታወቀ።

አገልግሎቱ ለጣቢያችን ኢቢኤስ በላከው መግለጫ ከ223 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ፕሮጀክቱን እያካሄደ ሲሆን፣ ዓላማውም በእርጅና ምክንያት ተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ የሚያስከትሉ መስመሮችን በማደስ አስተማማኝ አቅርቦት ማረጋገጥ ነው ብሏል።

አገልግሎቱ እስካሁን ከሆሳዕና እስከ ፎንቆ 32 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር፣ ከሆሳዕና እስከ አንጋጫ 28 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር፣ ከወልቂጤ እስከ እንድብር 31 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከወልቂጤ እስከ ጉብሬ መውጫ 24 ኪሎ ሜትር ተጠናቋል ብሏል።

በፕሮጀክቱ የእንጨት ምሰሶዎች በኮንክሪት ምሰሶዎች መተካታቸውን፤ ያረጁ ኮንዳክተሮችም በአዳዲስ መቀየራቸውን እና ይህም ብልሽትና የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ያግዛል ተብሏል።

አገልግሎቱ ከፊል ሥራቸው የተጠናቀቁ መስመሮች ወደ አገልግሎት የገቡ መሆኑን ገልጾ ቀሪው ሥራ በመጪው ታህሳስ ወር 2019 ዓ.ም. መጨረሻ ተጠናቅቆ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ላይ እንደሚውልም አሳውቋል።