የወጪ ንግድ ገቢ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 7.7 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የ 2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ላይ ነው።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢው የእቅዱን 121 በመቶ ያሳካ ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ 2,936,270 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
መረጃው ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
