ፋይዳና የባንክ ሂሳብ
የባንክ ሂሳባቸውን ከ”ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ጋር ሊያስተሳስሩ እንደሚገባ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አሳሰበ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም በተሰጠው የጊዜ ገደብ የፋይዳ መታወቂያቸውን ከባንክ ሲስተም ጋር ላላስተሳሰሩ ዜጎች አዲስ አበባን ጨምሮ በ26 ዋና ዋና ከተሞች የሚገኙ የባንክ ደንበኞች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲያስተሳሰሩ ማስታወቁ ይታወሳል።
በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ ደንበኞች ደግሞ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሂሳባቸውን ከፋይዳ ቁጥር ጋር አያይዘው ማጠናቀቅ እንደሚገባቸውም ተጠቅሷል።
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያሥላሴ ማኅበረሰቡ የመጨረሻ ቀንን የመጠበቅ ልማድ ስላለው ቀነ-ገደቡ በተደጋጋሚ እንዲራዘም መደረጉን አስታውሰው፤ ከዚህ በኋላ ግን ዕድሉ የመጨረሻ ሊሆን ስለሚችል ዜጎች ሳይዘናጉ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
