የዕጩ ወኪሎች ግዴታ
ማንኛውም ተዘዋዋሪም ሆነ ተቀማጭ የዕጩ ወኪሎች ግዴታ ምን ምን ናቸው?
👉የምርጫ ኃላፊው የሚሰጠውን ትዕዛዞች ማክበር አለበት፣
👉የምርጫ ሂደቱን ከሚያውኩ ተግባራት መቆጠብ አለበት፣
👉አግባብ ባለው አካል ሲጠየቅ መታወቂያውን ማሳየት አለበት፣
👉የምርጫ ሕጉን ማክበር አለበት፣
👉የምርጫውን ሂደት የመከታተል ተግባሩን ሲያከናውን መራጮች ማንን መምረጥ እንዳለባቸው አስተያየት ከመስጠት ወይም ተጽዕኖ ለማሳደር መሞከር የለበትም፣
👉የምርጫ ቁሳቁሶችን መያዝ፥ ማንሳት፤ መነካካት ወይም በቁሳቁሶቹ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ተግባራትን መፈጸም የለበትም፣
👉የምርጫ ጣቢያውን ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ከማስፈራራት ወይም ሥራውን ከሚያደናቅፉ ተግባራት መቆጠብ አለበት፣
👉ወደ ድምፅ መስጫ ክፍሎች መግባት የለበትም፣
👉ቦርዱ የሚያወጣውን የሥነ ምግባር ደንብ መፈረም እና ማክበር ይገባዋል፡፡
መረጃው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
