EthiopiaNews

የኢትዮጵያ እና የናይጄሪያ መንግሥታት የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸውን ታራሚዎች መለዋወጥ የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሕግ ትብብር ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ እርምጃ መሆኑም በስምምነቱ ወቅት ተነግሯል፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስትር ሃና አርአያስላሴ እና የናይጄሪያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና ፍትሕ ሚኒስትር ላቲፍ ኦላሱንካንሚ ፋግቤሚ ተፈራርመዋል፡፡

በፍትሕ ዘርፍ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የተፈረመው ስምምነቱ በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያሳድገው መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ከተፈረመው የፍርደኞች ማስተላለፍ ስምምነት በተጨማሪ በሌሎች የሕግ ጉዳዮች በትብብር ለመስራት ሁለቱ አገራት ዝግጁ መሆናቸውም ነው የተነገረው፡፡

ስምምነቱ በአግባቡ እንዲፈጸም ትኩረት መስጠት እንደሚገባ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተጠቆመ ሲሆን በዚሁ ወቅት የሁለቱም አገራት የፍትሕ ሚኒስትሮች ስምምነቱን ተፈጻሚ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት እና ዝግጁነት መግለጻቸውን ፍትህ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስፍሯል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews