የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከቀድሞ የኦሮሚያ ታጣቂዎች አጀንዳ መረከቡን አስታወቀ።
በኦሮሚያ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና በአሁኑ ሰዓት ሰላምን መርጠው የተመለሱ አካላት አጀንዳቸውን በተወካዮዎቻቸው በኩል በይፋ ለኮሚሽኑ አሰረክበዋል።
በአጀንዳ ርክክብ መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ብቸኛው የሰላም መንገድ ምክክር መሆኑን አምናችሁ በመምጣታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
ኮሚሽኑ የተረከበውን አጀንዳ በቅርቡ የሚያካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አካል እንደሚያደርገውም ገልፀዋል። መረጃው ከኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
