EthiopiaNews

የፕላስቲክ ከረጢት ሲያሰራጩ የተገኙ 41 የጅምላ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነግሯል

በአዲስ አበባ መርካቶ የገበያ ማዕከል የፕላስቲክ ከረጢት ሲያሰራጩ የተገኙ 41 የጅምላ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ፓሊስና ከከተማዋ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በቅንጅት ባካሄዱት የክትትልና ቁጥጥር ዘመቻ አከፋፋዮቹ በሀገሪቱ ትልቁ የንግድ ማእከል ከሆነው መርካቶ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የላስቲክ ከረጢት ሲያሰራጩ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በመሆኑም የፕላስቲክ ከረጢት አጠቃቀምን ለመገደብ በወጣው አዋጅ መሰረት አከፋፋዮቹ ክልከላ የተጣለባቸውን እና ለአካባቢ ብክለት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በስፋት ሲያከፋፍሉ በመገኘታቸው ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተብሏል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv