EthiopiaNews

ከወላይታ ሶዶ ወደ ገሳ ከተማ ሲጓዝ በነበረ ተሽከሪካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 4 ሰዎች ሞቱ።

አደጋው ልዩ ስሙ “ዛሮ ቁልቁለት” ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከሪካሪው በመገልበጡ ነው የደረሰው፡፡

በአደጋው 22 ሰዎች በፅኑ ሲቆስሉ እና 24 ሰዎች ደግሞ ቀላል አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል።

አደጋ የደረሰባቸው ተሳፋሪዎችም በወላይታ ሶዶ ክርስትያን ሆስፒታልና በኦቶና ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተነግሯል። መረጃው ከደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv