InternationalNews

የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ሞጅታባ ከሀሚኒ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት ተስፋ በመቁረጣቸው ነው ማለታቸው ተሰምቷል።

አያቶላ ባስተላለፉት መልዕክት የሀገራቸው ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን የኢራንን መብት ለማስጠበቅ ማረጋገጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ስምምነቱ እንዲተገበር ማዘዛቸውን ጠቁመው አሜሪካ ስምምነቱን የተቀበለችው በፍፁም ተስፋ መቁረጥ ነው ብለዋል፡፡

መንፈሳዊ መሪው አክለውም በሀገራቸውና በአሜሪካ መካከል በቀጣይ የፊት ለፊት ውይይቶች እንደሚኖሩ ጠቁመው ይህ ማለት ግን የጠላትን አቋም እንቀበላለን ማለት አይደለም ብለዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት የደረሱበትን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ ጥላው የቆየችውን እገዳ ስታነሳ ኢራን በበኩሏ የሆርሙዝ ሰርጥን ሙሉ ለሙሉ መክፈቷ ነው የተሰማው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሁለቱ ሀገራት መካከል ዛሬ በስዊዘርላንድ ይካሄዳል የተባለው የፊት ለፊት የፊርማ ስነ ስርዓት መሰረዙ የተነገረ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የአሜሪካና ኢራን መሪዎች በበይነ መረብ መፈራረማቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews