EthiopiaNews

ሚኒስቴሩ ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ጋር ተስማሚ የሆነ የሽያጭ መመዝገቢያ መጠቀምን አስገዳጅ የሚያደርግ መመሪያ አወጣ

ማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ መመዝገቢያ ደረሰኝ ሶፍትዌር አቅራቢ ወይም የክላውድ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ይህንን ተግባር ለማከናወን ፈቃድ ሲያወጣ እንደ ዋስትና በባንክ ወይም በመድን የተረጋገጠ እስከ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የመልካም አፈፃፀም ዋስትና እንዲያቀርብ የሚጠይቅ አዲስ መመሪያ ተዘጋጀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ያወጣው ይህ መመሪያ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት አስተዳደር መመሪያ የተሰኘ ሲሆን መመሪያው ማንኛውም የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ በሚኒስቴሩ እውቅና ከተሰጠው የሽያጭ መመዝገቢያ ሶፍትዌር ጋር የተገናኘ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ የመጠቀም ግዴታ እንዳለበት ተቀምጧል።

በዚህ መመሪያ መሰረት ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ተስማሚ የሆነ የሽያጭ መመዝገቢያ ስርዓት መጠቀም በሁሉም የሂሳብ መዝገብ በሚይዙ ታክስ ከፋዮች አስገዳጅ ሲሆን ትግበራው ባለስልጣኑ በሚያወጣው መርሐ ግብር መሰረት የሚተገበር ይሆናል ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv