በኢትዮጵያ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ 2 ትሪሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለ
ከአሁን በፊት የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እስከ 2 ትሪሊየን ብር እንደሚያስፈልግ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ ይህንን ትናንት የገለጹት የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀት ላይ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከባለበጀት መስሪያ ቤቶች ጋር የማጠቃለያ ውይይት ወቅት የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጓተትን አስመልክቶ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቶች ጥያቄ የሌለበት አካባቢ የለም ያሉት ሚኒስትሩ ከአሁን በፊት የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ብቻ እስከ 2 ትሪሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ገልጸው ፤ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚያስፈልጉትን በመለየት ደረጃ በደረጃ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በመድረኩ የ2019 የበጀት አመዳደብ ዕቅድ የራስን ወጪ በራስ አቅም ለመሸፈን ታልሞ የተዘጋጀ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን 80 በመቶውን በጀት ከሀገሪቱ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱም ሰምተናል፡፡
ምክር ቤት በዛሬው ውሎው የመጨረሻውን የ2019 የበጀት አመዳደብ ዕቅድ ውይይት ያካሄደ ሲሆን ውይይቱን በማታው የዜና ክፍለ ጊዜያችን የምንመለስበት ይሆናል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
