EthiopiaNews

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መረጃዎች

 🔸እስካሁን ባለው የምርጫ ሂደት 50 ሺ 188 የምርጫ ጣቢያዎች በሰዓቱ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

🔸የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሀይሉ የምርጫ ሂደቱን አስመልክቶ የመጀመሪያውን የዕለቱን መግለጫ በሰጡበት ጊዜ 695 ምርጫ ጣቢያዎች በሰዓቱ አለመከፈታቸውን ነው የገለፁት።

🔸143 የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ በፀጥታ ችግር ምክንያት እንዳልተከፈቱ ሰብሳቢዋ ገልጸዋል፡፡

🔸ይህም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በሚገኙ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች በምርጫ ወቅት ባጋጠመ የፀጥታ ችግር ምክንያት መከሰቱና በዚህም የምርጫ ሂደቱ መቋረጡን ነው ያመለከቱት።

🔸ሰብሳቢዋ አክለውም በተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች 39 ሺ 732 ታዛቢዎች መገኘታቸውን አሳውቀዋል።

#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv